የአማራ ክልሉ ፕሬዚዳንት ተብዬ አቶ አረጋ ከበደ ላሊበላ ላይ ጥቃት ተፈፀመባቸው!

የአማራ ክልሉ ፕሬዚዳንት ተብዬ አቶ አረጋ ከበደ ላሊበላ ላይ ጥቃት ተፈፀመባቸው!

በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ተከዜ ክፍለ ጦር  3ኛ ሻለቃና የክፍለ ጦሩ ሜካናይዝድ በጋራ  በመሆን ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 እስከ  ረፋዱ 3:30 ሰዓት  በወሰዱት ጥቃት የክልሉ ፕሬዝዳንት ነኝ የሚሉት አቶ አረጋ ከበደ ከባህርዳር ኤርፖርት በመነሳት ላሊበላ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ወደ ላሊበላ ከተማ በማቅናት ላይ እያሉ ሹምሽሃ አየር ማረፊያ አጠገብ ልዩ ስሙ በርታ በተባለ ቦታ ድንገተኛና የተጠና ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል።

በተወሰደባቸውም መብረቃዊ ጥቃት ከ10 በላይ ቀይ ቦኔት ለባሽ አጃቢዎቻቸው የተደመሰሱባቸው ሲሆን ፕሬዝዳንቱም ለጥቂት ከፋኖ በትር እንዳመለጡና ከአየር ማረፊያው ቅርብ እንደነበሩ እና መንገድ ቀይረው በሌላ አቅጣጫ ፈርጥጠዋል ሲል የምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አሳውቋል።

በመጨረሻም አገዛዙ ብልፅግና የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንደሚገኝና የአለባብሰው ቢያርሱ የአዳራሽ ዲስኩር ህዝቡን እንደማያደናግረውና የፋኖ የድል ችቦና የአማራ ህዝብ ሰቆቃ የሚያበቃበት  ዘመን እውን እየሆነ መምጣቱን የተከዜ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ኮማንዶ ዘላለም ሲሳይ ገልጿል።