በደሴ ዙሪያ ወረዳ አጥንት መስበሪያ እና እሁዲት ተብለው በሚጠሩ አከባቢዎች ላይ በተደረገ ውጊያ የፀረ አማራው ብልፅግና ቡድን ተላላኪ የሆኑ በርካታ ቁጥር ያላቸው የመከላከያ ሰራዊት፣ የአድማ ብተናና የሚኒሻ አባላት ሲገደሉ፣ በርካቶች መቁሰላቸውን በአፋብኃ የምኒልክ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ አስታውቋል።
አፋብኃ ምኒሊክ ዕዝ በላጎ ተወርዋሪ ሻለቃና ጥቅምት 27/2018 ዓ/ም የተመረቁት አዲሶቹ የልዩ ኮማንዶ አባላት በጋራ በመሆን ነው በጠላት ላይ ከባድ እርምጃ በመውሰድ ድሉን የተቀዳጁት ብሏል ዕዙ ለጣቢያችን በላከው መረጃ።
ከወደ ፋኖ የተሰነዘረበትን ጥቃት መቋቋም ያልቻለው ሙትና ቁስለኛ ከመሆን የተረፈው የጠላት ኃይል ወደ ኩታበርና ደሴ መፈርጠጡንም የዕዙ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለመረብ ሚዲያ በላከው መረጃ ጨምሮ ገልጿል