ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት ሕወሃት መሣሪያ እንዲደብቅና ተዋጊ እንዲያሠለጥን አይፈቅድም በማላት ዛሬ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሠጡት ምላሽና ማብራሪያ ላይ ተናግረዋል። ዐቢይ፣ መሣሪያ ደብቆ ማስቀመጥም ሆነ በኮንትሮባንድ ማስገባት በስምምነቱ ላይ የለም በማለት የሕወሓት አመራሮች ስምምነቱን እየጣሱ መኾኑን በመግለጽ ወንጅለዋል። ከውጭ አገራት ጋር ግንኙነት ማድረግ የፌደራል መንግሥቱ ሥልጣን ብቻ ሆኖ ሳለ፣ የሕወሓት ሰዎች ግን ከውጭ መንግሥታት ጋር ምን እየሠሩ ነው? በማለትም ዐቢይ ጠይቀዋል። ዐቢይ፣ ትግራይ እና አማራ ክልሎች የሚወዛገቡባቸው አካባቢዎች እጣ ፋንታ “በሕዝበ ውሳኔ” መወሰን እንዳለበትም ገልጸዋል።