ዐቢይ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ሩሲያ፣ አውሮፓ ኅብረት እና አፍሪካ በወደብ ጉዳይ ላይ የአሸማጋይነት ሚና እንዲጫወቱ ጠየቁ

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በባሕር በር ሳቢያ ጦርነት ከተቀሰቀሰ “ማንም አያስቆመነም” በማለት ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ላይ አስጠንቅቀዋል። ዐቢይ የኢትዮጵያ አቅም አስተማማኝ መሆኑን በመጠቆምም፣ ውጊያ ከተቀሰቀሰ “ውጤቱ ግልጽ ነው” በማለት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የቀይ ባሕርን ባለቤትነቷን ያጣችበት ውሳኔ በካቢኔ፣ ምክር ቤት ወይም ሕዝበ ውሳኔ የተላለፈ እንዳልኾነ የጠቀሱት ዐቢይ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ሩሲያ፣ አውሮፓ ኅብረት እና አፍሪካ በጉዳዩ ላይ የአሸማጋይነት ሚና እንዲጫወቱና ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያስገኙ ጠይቀዋል።