ብልፅግና በአዲስ አበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ።

አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ።

ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉ ታዉቋል።

በ11 ክፍለከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታፍሰዉ በሶስት መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉን ከአዲስአበባ  ከተማ ኗሪዎች ተናግረዋል።

በተለይ እድሚያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዉ ስለመወሰዳቸዉ ጭምር ኗሪዎች ተናግረዋል።

አፈሳው በናዝሬት፣በደብረዘይት፣በሞጆ፣በሀዋሳ፣በይርጋለም፣በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች እንዲሁም በጋሞ እና ወላይታ ብዛት ያላቸዉ ወጣቶች ታፍስዉ በእየ አዳራሹ ታጉረዉ ይገኛሉ።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚታፈሱ ወጣቶች ቁጥር ከወትሮው በተለየ መልኩ መጨመሩ የተገለፀ ሲሆን የብልግና ኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ የኦሮሞን ስልጣን እንጠብቅ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነትን ሊያጠፉ ነዉ በሚል ስብከት ወጣቱ እየታፈሰ ነዉ ተብሏል።