በጅማ ከተማ ቤታቸው ለኮሪደር ልማት የፈረሠባቸው ነዋሪዎች እየተንገላቱ መሆኑን ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን በጅማ ከተማ ቤታቸው ለኮሪደር ልማት የፈረሠባቸው ነዋሪዎች መንግሥት በተከራየላቸው የሆቴል አልጋዎች፣ በግለሰብ መኖሪያዎችና በቀበሌ ቤቶች ውስጥ እየተንገላቱ መኾኑን ተናግረዋል።

በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ግራና ቀኝ ያሉ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ለኮሪደር ልማቱ መፍረሳቸውን ምንጮች ተናግረዋል።

ከፈረሱት ቤቶች መካከል፣ አብዛኞቹ ሕጋዊ ካርታ ያላቸውና ግብር ከፋይ እንደነበሩ የጠቀሱት ምንጮች፣ ለፈረሱት ቤቶች ባለቤቶች መንግሥት የገንዘብ ካሳም ይኹን ተለዋጭ ቦታ አልሠጣቸውም ብለዋል።

በኮሪደር ልማቱ የፈረሱት ቤቶች 15 ሺሕ ገደማ እንደኾኑ ይታወቃል።