ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከ50 በመቶ በላይ የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች ከተቋማዊ መዋቅር ጋር በተያያዘ መዘጋታቸውን ከተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ባኹኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉት የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች 565 ገደማ ሲኾኑ፣ ከ540 በላይ የሚኾኑት ግን እንደተዘጉ መረዳት ተችሏል።
በአዲስ አበባ ከ116 የፖስታ ቤት ቅርንጫፎች 33ቱ ብቻ እንደቀሩ ምንጮች ተናግረዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ነባር የተቋሙ ሠራተኞችም ተቀንሰዋል ተብሏል።
ኾኖም ድርጅቱ ያሠራው መዋቅር እስካኹን ለሠራተኞች ይፋ እንዳልተደረገ ምንጮች ገልጸዋል።