አሜሪካ፣ መቀመጫውን ጀኔቫ ካደረገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ዛሬ ልትወጣ እንደኾነ ተሠምቷል።
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህን ትዕዛዝ የሚያስተላልፉት፣ ምክር ቤቱ በእስራኤል ላይ ከመጠን በላይ ትኩረት ያደርጋል፤ ለሌሎች ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ፈጻሚ መንግሥታት ሸፋን ይሠጣል በማለት እንደኾነ ፖለቲኮ ጋዜጣ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በመጀመሪያው የሥልጣን ዘመናቸው አሜሪካን ከሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤቱ አስወጥተዋት የነበር ቢኾንም፣ ተተኪያቸው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሜሪካን ወደ ምክር ቤቱ እንደመለሷት ይታወሳል።
ምክር ቤቱ፣ በዓለም ዙሪያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን በመከታተል የጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ያደርጋል።