የሶሻል ሚዲያ አትኩሮት የተነፈገውእኩለ ሌሊት የተጠናቀቀው የገዥው ብልጽግና ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ፣ ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከመረጣቸው 45 አባላት መካከል 18ቱ አዲስ ተመራጮች ኾነዋል።
ሠማ ጥሩነህንና ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የአማራ ክልል የፓርቲው ቅርንጫፍን ወክለው የነበሩ አምስት አባላት ተነስተው፣ በምትካቸው ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደንና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴንን ጨምሮ አዳዲስ አባላት ተመርጠዋል።
የኦሮሚያን የፓርቲው ቅርንጫፍ ወከለው ከቆዩት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መካከል ደሞ፣ ዐለሙ ስሜ እና ቢቂላ ሁሪሳ ተነስተው በአዲስ አባላት ተተክተዋል። ጉባኤው፣ ባስቀመጠው ኮታ መሠረት ከየክልሉ የፓርቲው ቅርንጫፍ የተውጣጡ 225 የምክር ቤት አባላትንም መርጧል። ብልታግ ና ስብሰባው እንደ አጀንዳ ያራገብልናል ብሎ ቢያስብም ሶሻል ሚዲያው አትኩሮት ነፍጎታል።