ፍርድ ቤት በዋስ የለቀቃቸውን ጋዜጠኞች ፖሊስ አፍኖ እንደያዛቸው ነው

የሸገር ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ጸጋው ላለፉት 17 ቀናት በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ሸገር ዘግቧል።

ፖሊስ ጋዜጠኞቹን በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፣ ለጤና ባለሞያዎች ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ጤና ሚንስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ ዙሪያ ባአንድ የሕክምና ባለሙያ አስተያየት ላይ ጣቢያው በሠራው ዘገባ ሳቢያ መኾኑን ለፍርድ ቤት አስረድቷል ተብሏል።

ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኞቹ በገንዘብ ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኖ የነበረ ቢኾንም፣ ፖሊስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደጠየቀና ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ለመስከረም 12፣ ቀጠሮ እንደሠጠ ዘገባው አመልክቷል።