በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ ሰኞ’ለት ታጣቂዎች በፈጸሙት “ሐይማኖት ተኮር” ጥቃት ሁለት የኦርቶዶክስ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመናን መገደላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ዘግቧል።
“ሐይማኖት ተኮር” ነው በተባለው ጥቃት፣ ከበደ ማሞ የተባሉ የ65 ዓመት አዛዉንትና የ6 ልጆች አባት እንዲሁም አበሬ ስዩም የተባሉ የሁለት ልጆች እናት በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን የዜና ምንጩ ከነዋሪዎች መስማቱን ጠቅሶ አስነብቧል።
ከሳምንታት በፊት በዞኑ ሮቤ ወረዳ የመሰራንጄ ኦዳ ቅዱስ ጊዎርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ መምሬ ንጉሤ ወልደ መድኅን ካህን በመኖሪያ ቤታቸው በታጣቂዎች በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ይታወሳል።