የኬንያ ፓርላማ አባል የሆኑት ፋራህ መዓሊም፣ ኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይን ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግሥታት በቀጠናው ያራምዱታል ያሉትን የማናለብኝነት ፖሊሲ ለመመከት፣ የጋራ ወታደራዊ ትብብር ስምምነት እንዲፈራረሙ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሠፈሩት መልዕክት ጥሪ አድርገዋል።
ኢትዮጵያን ከእስራኤል ጋር ያመሳሰሉት መዓሊም፣ ኢትዮጵያ ልክ እንደ እስራኤል “በሐሰት ታሪክ እና በምዕራባዊያን ያልተቆጠበ ድጋፍ አቅሏን ስታለች” በማለት ተችተዋል።
መዓሊም፣ ከሶማሊያ ጋር የምትዋሰነውን የኬንያዋን ጋሪሳ ግዛት የሚወክሉ የፓርላማ አባል ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ በተደጋጋሚ የከረረ ትችትና ተቃውሞ በማቅረብ ይታወቃሉ።