“ቢራቢሮ መቀመጫዋን መሸፈን ሳትችል፣ መሬት ትሸፈናለች” ሲል ሻዕቢያ በብልፅግና ላይ ተሳለቀ

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር፣ የኢትዮጵያው ገዥ ፓርቲ ባለስልጣናት፣ በባሕር በር ዙሪያ የሚያራምዱት ትርክት “ቢራቢሮ መቀመጫዋን መሸፈን ሳትችል፣ መሬት ትሸፈናለች” የሚለውን አገራዊ ብሂል የሚያስታውስ ነው በማለት ተሳልቋል።

ሚንስቴሩ፣ የብልጽግና ፓርቲ ባለስልጣናት ሕገወጡን የባሕር በር አጀንዳ ትክክለኛ ብሄራዊ አጀንዳ ለማስመሰል መጠነ ሰፊ ዘመቻ ያደርጋሉ ብሏል። ትርክቱ በኢትዮጵያና በጠቅላላው በቀጠናው ላይ አለመረጋጋት ያስከትላል ያለው ሚንስቴሩ፣ ኤርትራ ከጎረቤቶቿ ጋር ትብብር ማድረግ የምትችለው በመከባበር፣ በግልጽ ሕጋዊ መሠረትና ለቀጠናዊ መረጋጋት በጋራ በመስራት ብቻ ነው በማለት የመንግሥትን አቋም አስፍሯል።

ሚንስቴሩ፣ የብልጽግና ፓርቲ የባሕር በር አጀንዳ “ሃላፊነት የጎደለው”፣ “የማያዛልቅ”፣ ውድቅ ሊደረግና ሊመከት የሚገባው መኾኑንም ጠቅሷል።