ሰበር!…..ከባድ ተኩስ በወልድያ ከተማ!
የሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ በሆነችው ወልድያ ከተማ ከምሽቱ 5:35 ጀምሮ ለደቂቃዎች የቆየ ከባድ የተኩስ ድምፅ መሰማቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለመረብ ሚዲያ ገልፀዋል።
የተኩስ ድምፁ የተሰማው በከተማዋ አዳጎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው የአድማ ብተና ካምፕ ውስጥ ነው ተብሏል።
አሁን ላይ ተረጋግቷል የሚሉት የመረብ ምንጮች፡ ነገር ግን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ላይ የአምቡላንስ እንቅስቃሴ ይታያል ብለዋል።
የዞኑ ካድሬዎች የሕዳሴ ግድብ መመረቁን ሰበብ በማድረግ በከተማዋ መንግስትን የሚደግፍ የግዳጅ ሰልፍ ለነገ መጥራታቸውን መረብ ሚዲያ ከሰዓታት በፊት መዘገቡ ይታወሳል።
የብልፅግናው ቡድን እራሱ ባደራጃቸው ሽብር ፈጣሪ አካላት በአማራ ክልል በተመረጡ ከተማዎች ለነገ በጠራው የግዳጅ ሰልፍ ላይ ቦምብ በማስወርወር “ፋኖ ጥቃት ፈፀመ” በሚል ሐሰተኛ መረጃ ለማሰራጨት ዝግጅት ስለማድረጉ ለጣቢያችን የደረሰው መረጃ ያመላክታል።