ፀረ ህዝብ የሆነዉ ብልፅግና በእስቴ መካነየሱስ ከተማ አሰቃቂ ተግባር መፈፀሙ ተሰማ!!
የእስቴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ማንተፋርዶ ሞላ የተባለ ሆድ አደር ባንዳ የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ኮር አንድ ጉና ክፍለጦር አስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ ሁለት ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታርቆ ታመነ ቤትን በቦንብ በመምታት በቤቱ ላይ ከባድ ጉዳት እንዲደርስ ተደርጓል።
በእስቴ መካነየሱስ ከተማ ቀበሌ01 የሚገኘውን መኖሪያ ቤት ከሌሊቱ 6 :00 ሰአት ቤቱ ውስጥ የሚገኙትን ሰወች እንደተኙ በስከውጭ እንዳይወጡ በመቆለፍ ቤቱን በጋዝ በማርከፍከፍ በቦንብ ጭምር ቤቱ እንዲቃጠል አድርገውታል።
6 ሰው የአርበኛ ቤተሰቦች እብረው እንዲቃጠሉ ከተፈረደባቸው የሞት ፍርድ በእሪታ አካባቢ ሰው ደርሶ አትርፏቸዋል።
በከተማዋ የሚፈፀሙ አሰቃቂ ድርጊቶች ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን የሚፈፀሙ አሰቃቂ ግፎችን በበላይነት የሚፈፅመዉ የወረደው አስተዳዳሪ አቶ ማንተፋርዶ ሞላ ነዉ።