አብዲራህማን መሃዲ የሚመሩት የኦብነግ አንጃ፣ የሶማሌ ክልል መንግሥት አንድ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሉን ጨምሮ አራት ከፍተኛ አመራሮቹን ጅግጅጋ ውስጥ በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ላይ እንዳሠረ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።
በክልሉ መንግሥት ትንኮሳ ወደ ጦርነት ተገደን አንመለስም ያለው አንጃው፣ ቡድኑ በሰላማዊ ትግሉ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል።
አንጃው አያይዞም፣ የሶማሌ ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ ለመወሰን፣ ለፍትሕና ዲሞክራሲ የሚያደርገውን ትግል በኃይል መጨፍለቅ አይቻልም ብሏል።
የክልሉ መንግሥት የአሥመራውን የሰላም ስምምነት በመጣስ፣ በክልሉ በተለይም በኦጋዴን ዳግም የትጥቅ ግጭት እንዲቀሰቀስ በማድረግ ላይ ይገኛል በማለት አንጃው በተደጋጋሚ ሲከስ ቆይቷል።