በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ በአገሪቲ ሰላምና መረጋጋት እንዲኹም በቀጠናው ላይ የደቀነው ስጋት አኹንም ቀጥሏል ( ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ )

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ኹኔታ በአሜሪካ “ብሄራዊ ደኅንነት” እና “የውጭ ፖሊሲ” ላይ “ያልተለመደ” እና “ልዩ የኾነ ስጋት” ደቅኗል በማለት ከአራት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፉትን ፕሬዝዳንታዊ የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ድንጋጌ ሰሞኑን ለአንድ ተጨማሪ ዓመት አራዝመውታል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፕሬዝዳንታዊውን የአስቸኳይ ጊዜ ኹኔታ ድንጋጌ ያራዘሙት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ኹኔታ በአገሪቲ ሰላምና መረጋጋት እንዲኹም በቀጠናው ላይ የደቀነው ስጋት አኹንም ቀጥሏል በማለት ነው።

ፕሬዝዳንታዊ ድንጋጌው፣ በጦርነቱ ወቅት ተፈጽመዋል በተባሉ “የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች” እና “የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተጓጎል” ወንጀሎች በተጠረጠሩ ማንነታቸውና ቁጥራቸው ባልተጠቀሰ የተወሰኑ ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ የጣለ ነው።