ዙ23ና ዲሽቃ በታጠቀ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሰራዊት ታጅበው ከማክሰኝት ወደ አዘዞ ሲጓዙ በነበሩ የአገዛዙ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ከባድ የደፈጣ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ!
ወታደራዊ አመራሮቹ ከፍተኛ ቁጥር ባለውና ከዙ23 ጀምሮ እስከ ዲሽቃ መሣሪያ በታጠቀ ሰራዊት ታጅበውም ከፋኖ ጥቃት ባለመትረፋቸው “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” በሚል የተተረቡ ሲሆን፡ በተጨማሪም የትኛውም ሰራዊትና ከባድ መሣሪያ ከፋኖ እንደማያድናቸው በግልፅ ያሳየ ነው ተብሏል።
በማዕከላዊ ጎንደር መነሻቸውን ከማክሰኝት ከተማ አድርገው ዙ23ና ዲሽቃ መሣሪያ በታጠቀ ከፍተኛ ቁጥር ባለው ሰራዊት ታጅበው ወደ አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ ሲጓዙ የነበሩ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች፡ ልዩ ስሙ ምንዝሮ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ላይ ከባድ የሆነ ደፈጣ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው መረብ ሚዲያ ከአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ለማረጋገጥ ችሏል።
ይሄንን የተመለከቱ የአከባቢው ነዋሪዎች፦
“ወይ መድፍ ብላሽ ወይ ድሮን ብላሽ፡
ወይ ሞርተር ብላሽ ወይ ታንክ ብላሽ፡
አፈር አስጋጠው ፋኖ በክላሽ”
በሚል ሲተርቡ አርፍደዋል።
ደፈጣ ጥቃቱ የተፈፀመው ዛሬ ጳጉሜ 03/2017 ዓ/ም ማርፈጃውን ሲሆን፡ እርምጃውን የወሰዱት በአፋብኃ በላይ ዘለቀ ዕዝ ዳግማዊ ቴዎድሮስ ኮር ጎንደሬ በጋሻው ከ/ጦር ስር የሚገኙት “ፀያይሞቹ አናብስቶች”የሚል ቅፅል ስም የተሰጣቸው የሻለቃ ዋሴ ተኮላ ብርጌድ አባላት መሆናቸው ታውቋል።
በዚህ ደፈጣ ጥቃት፡ ታጅበው ሲጓዙ በነበሩ ወታደራዊ አዛዦች ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ በግልፅ ባይታወቅም፡ ነገር ግን አዛዦቹን አጅበው ከነበሩ ወታደሮች መካከል በርካቶች ሙትና ቁስለኛ መደረጋቸውን ዕዙ በሕዝብ ግንኙነት መምሪያው በኩል ባወጣው መረጃ ገልጿል።
ወታደራዊ አመራሮቹ ከፍተኛ ቁጥር ባለውና ከዙ23 ጀምሮ እስከ ዲሽቃ መሣሪያ በታጠቀ ሰራዊት ታጅበውም ከፋኖ ጥቃት ባለመትረፋቸው “የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም” በሚል የተተረቡ ሲሆን፡ በተጨማሪም የትኛውም ሰራዊትና ከባድ መሣሪያ ከፋኖ እንደማያድናቸው በግልፅ ያሳየ ነው ተብሏል።