የግዕዝ ቋንቋ እንደ አንድ ትምህርት እንዲሰጥ ዝግጅት ተደርጓል ተባለ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በቀጣዩ የትምህርት ዘመን በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከሦስተኛ ክፍል ጀምሮ የግዕዝ ቋንቋ እንደ አንድ ትምህርት እንዲሰጥ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል። ቢሮው በቂ የግእዝ መምህራን ለመመደብና የመማሪያ መጽሐፍትን ለማሰራጨት ዝግጅት ማድረጉን መስማቱን ጠቅሶ የዘገበው ደሞ ቢቢሲ ነው። እስከ ስድስተኛ ክፍል በቂ የማስተማሪያና መማሪያ መጽሐፍትም ለሕትመት ተዘጋጅተዋል መባሉንም ዘገባው ጠቅሷል። የመምህራን እጥረት እንዳይፈጠር በ2018 የትምህርት ዘመን በተመረጡ ኮሌጆች በቋንቋው መምህራንን ለማስመረቅ ዝግጅት እንደተደረገም ተገልጧል።