መንግስታዊ ዝርፊያ! ( የኦሮሚያ ክልል ጉድ )

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የቤት ግብር ክፈሉ ይላችሁና እሺ ብላችሁ ልትከፍሉ ስትሄዱ የቤት ግብሩን ብቻ ብትከፍሉ አይቀበላችሁም።
አመናችሁበት አላመናችሁበት፣ ይጥቀማችሁም አይጥቀማችሁ ተጨማሪ ክፍያዎችን በግዳጅ እንድትከፍሉ ትደረጋላችሁ።
ለምሳሌ የእኔ የቤት ግብር የተገመተው 15,153.60 ብር ነው። ነገር ግን የሚከተሉትን ክፍያዎች በአስገዳጅ እንድከፍል ተደርጊያለሁ:-
1) የጤና መድህን አልተመዘገብኩም ወይም ተጠቃሚ አይደለሁም ነገር ግን 1,310 ብር እንድከፍል ተገድጃለሁ።
2) እስከማቀው ድርስ የሌላ ሀገር ዜጋ በኢትዮጵያ ውስጥ ሲኖር የተወሰነ ገንዘብ እንዲከፍል ይደረጋል እንጂ ዜጋው የሚከፍለው ገንዘብ የለም። በኦሮሚያ ውስጥ ግን የዜግነት 3,000 ብር ይከፈላል። ያውም ከኦሮሞ ውጪ የሆነ ሰው ይህ ነው የሚባል መብት ሳይኖረው።
3) ቡሳ ጎኖፋ (ለተማሪዎች ምገባ) 1,000 ብር ይከፈላል። ተማሪ የሚመገበው ዜጎች ከከፈሉት ግብር ላይ እንጂ በተጨማሪ ዜጎች ተገደው እንዲከፍሉ በማድረግ አይደለም።
4) የኦሮሚያ ልማት ማህበር አባል አይደለሁም ነገር ግን በግድ 500 ብር እንድከፍል ተደርጊያለሁ።
5) የቀይ መስቀል ማህበር አባል አይደለሁም ነገር ግን 500 ብር እንድከፍል ተደርጊያለሁ።
6) የስፖርት ደጋፊም ነቃፊም አይደለሁም ነገር ግን 500 ብር ተወስዶብኛል።
በጥቅሉ 24,963.60 ብር እንድከፍል ሲደረግ ከዚህ ውስጥ 9,810 ብር ሳላምንበት በጉልበተኛ መንግስት የተዘረፍኩት ነው።
(Edeltu Afar) ደረሰኞቹ ከታች ይመልከቷቸው