” በህግ እንጂ በሀይል አንገዛም ! ” – የመኾኒ ከተማ ነዋሪዎች
➡️ ” ምርጫችን ሽፍቶች ህዝብ ይዘው እንዲጠፉ መፍቀድ ወይስ ለሞትና ስደት የዳረጉንን ማስወገድ ? ” አቶ ጌታቸው ረዳ
በትግራይ ደብባዊ ዞን ራያ ዓዘቦ ወረዳ መኾኒ ከተማ በታጣቂዎች መካከል በተከፈተ ቶክስ 8 ስቪሎች መቁሰላቸው ተከትሎ ቁጣ የተቀላቀለበት ስልፍ ዛሬ ተካሂደዋል።
በርካታ ወጣቶችና እናቶች የተተሳተፋበትና ፓሊስ ስርዓት ያስከበረበትን ሰልፍ የከተማው አስተዳደር እንደጠራው ነው የተሰማው።
ነዋሪዎቹ ዛሬ ከሰዓት በኃላ ባካሄዱት ቁጣ የተሞላበት ሰልፍ የትግራይ ኃይል (ቲዲኤፍ) ከከተማቸው እንዲወጣ ጠይቀዋል።
ሰልፈኞቹ ፦
– በህግ እንጂ በሀይል አንገዛም !
– ሰላማዊ ሰዎች መጨፍጨፍ ይቁም !
– በሀይል የሚጫንብን አስተዳደር አንቀበልም !
– ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችን አሳልፈን አንሰጥም !
– የሀይል አገዛዝ እንኮንናለን !
– አንድ ቡድን ስልጣን ላይ እንዲቆናጠጥ አልሞ የሚካሄድ ጭፍጨፋ አንኮንናለን !
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አስምተዋል።
ዛሬ ሰልፉ ተከትሎ የተፈጠረ ግጭት እንደሌለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች አረጋግጠዋል።
ሰሞነኛውን ሁኔታ በተመለከተ የቀድሞ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ” በመኾኒ ሰላማውያን ሰዎች ላይ የተፈፀመ የአመፅ ተግባር በኔትወርክ የተደራጀው የወንጀለኞች ቡድን በትግራይ ህዝብ ላይ ሲፈፅመው የቆየውና በቀጣይ ሊያደርገው ያቀደው ተቀጥያ ነው ” ብለዋል።
” በጥቂት ለሚቆጠሩ ኃላቀሮች ተብሎ ህዝብ እንደ ህዝብ ቢያልቅ ግደ የሌለው ቡድን ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የባሰ እልቂት ማስከተሉ አይቀሬ ነው ” ሲሉ ገልጸዋል።
” ምርጫችን ሽፍቶች ህዝብ ይዘው እንዲጠፉ መፍቀድ ወይስ ለሞትና ስደት የዳረጉንን ማስወገድ ? ” የሚል ጥያቄ ያነሱት አቶ ጌታቸው ” እድሜ ልኩ ውይይትና ሰላማዊ መፍትሄ የሚባል ቋንቋ የማይገባው የስርቆትና የአፈና መሃንዲስ ” ሲሉ በስም ሳይጠቅሱ ያብጠለጠሉት አካል ” ይብቃው ” ብለውታል።