በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ በዛሬው ዕለት ቀኑን ሙሉ ከመጠን በላይ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ  የሶስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ሰለባ የሆኑ ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው የተባለ ሲሆን አደጋው ፍንጫዋ በተባለ ፏፏኔ አጠገብ ለሣር አጨዳ በሄዱበት መከሰቱ ተገልጿል።

በአደጋው ምክንያት ህይወታቸው ካለፉት መካከል የአንዲት ሴት ልጅ አስከሬን መገኘት ችሏል። ሆኖም የእናት እና የወንድ ልጅ አስክሬን ግን ባለመገኘቱ የአከባቢ ማኅበረሰብና የፀጥታ አካላት ፍለጋ ላይ ይገኛሉ።

በወረዳው በአደጋ ቀጠና ስር ያሉ ሰዎችን  እንደዚህ ዓይነትና ሌሎች አደጋዎች እንዳይርስባቸው ወደ ሌላ ቦታ የማሸጋገር ሥራዎች እየተሱሩ ይገኛሉ ሲል የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።