አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ያካተታቸውን ድንጋጌዎች እንዲያነሳ ጠይቋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ በተሻሻለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ረቂቅ አዋጅ ያካተታቸውን ድንጋጌዎች ባስቸኳይ እንዲያነሳ ጠይቋል።

ተቋሙ፣ የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚንስቴር አዋጁን የማሻሻል ሂደት በከፍተኛ ሚስጢር እንደያዘውና በማሻሻያው ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶች በጣም ውስን እንደኾኑ በመጥቀስም ተችቷል።

መንግሥት ማሻሻያውን እንዲተው የልማት አጋሮች ግፊት እንዲያደርጉ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የመደራጀትና የመሰብሰብ መብት እንዲከበርና በመብት ተሟጋቾች፣ በጋዜጠኞችና በማኅበረሰብ አንቂዎች ላይ የሚወሰዱ ርምጃዎች እንዲቆሙ የጠየቀው ተቋሙ፣ የልማት አጋሮች በአገሪቱ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ የሚያደርጉትን ክትትል እንዲያጠብቁም ጥሪ አድርጓል።