የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ጥያቄና የሥራ ማቆም አድማ አስተባባሪ ቡድን፣ የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ ከደመወዝ ጋር ብቻ የተያያዘ እንዳልኾነ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት አስታውቋል።
የጤና ባለሙያዎች አጣዳፊ ጥያቄዎች የኾኑት የትርፍ ሰዓትና የጉዳት ክፍያና የመኖሪያ ቤት ድጎማ አኹንም ምላሽ እንደሚፈልጉ ቡድኑ ገልጧል። ቡድኑ፣ እነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ እስካላገኙ ድረስ የደመወዝ ማስተካከያው ምሉዕ ሊኾን አይችልም ብሏል።