አብን የግብፁን አልሲሲን ሲያስጠነቅቅ ብልፅግናን መረጃ ስጠኝ ብሏል

አብን፣ መንግሥት የውጭ አካላት በአገሪቱ ላይ በሚፈጥሩት ስጋት ዙሪያ ግልጽና ወቅታዊ መረጃ እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል። አብን፣ መንግሥት ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ ደኅንነት ሕዝቡ ያለውን ድጋፍ እንዲያስተባብር፣ የውስጥ ግጭቶችን በንግግር እንዲፈታና በሉዓላዊነት ላይ የሚቃጡ ስጋቶችን በጥብቅ እንዲከታተልና እንዲያጋልጥም አሳስቧል። ሕዝቡ ግድቡን ከወገንተኛ ፖለቲካ፣ ከውስጣዊ ልዩነቶች ወይም ከግጭቶች በላይ መሆኑን እንዲገነዘብም ፓርቲው አሳስቧል። አብን፣ የግብጹ ፕሬዝዳንት አል ሲሲ ግብጽ በናይል ወንዝ ላይ አለኝ የምትለውን የውሃ ድርሻ አሳልፋ እንደማትሰጥና በዓለማቀፍ ሕግ ያላትን መብት ተጠቅማ ማናቸውንም ርምጃ እንደምትወስድ ሰሞኑን የሰሙትን ማስጠንቀቂያም አውግዟል።