ኢትዮጵያ፣ ከጅቡቲ፣ ከኬንያና ሶማሌላንድ ጋር በተያዘው በጀት ዓመት በየብስ ትራንስፖርት ለመገናኘት ቁርጠኛ አቋም እንዳላት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚንስትር ደኤታ ባረኦ ሐሰን መናገራቸውን ሚንስቴሩ ባሠራጨው መረጃ አስታውቋል።
ባረኦ ይህን ያስታወቁት፣ መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው የ”አቢሲኒያ ሌግዠሪ ኮች” የግል የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤቶችንና አመራሮችን ሰሞኑን በጽሕፈት ቤታቸው ባነጋገሩበት ወቅት እንደሆነ ተገልጧል።
በቅርቡ ከናይሮቢ-አዲስ አበባ የሙከራ የአውቶብስ ትራንስፖርት የጀመረው “አቢሲኒያ ላግዠሪ ኮች” ኩባንያም አስፈላጊውን ሂደት አሟልቶ እንዲቀርብ ከስምምነት ላይ እንደተተደረሰ ተገልጧል።