አብዲራህማን መሃዲ የሚመሩት የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) አንጃ፣ የሶማሌ ክልል ጸጥታ ኃይሎች ጅግጅጋ ውስጥ ሴቶችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላቱን ሐሙስ፣ ነሃሴ 8፣ 2017 ዓ፣ም እየደበደቡ በመውሰድ አስረዋል በማለት ከሷል።
አንጃው፣ ጸጥታ ኃይሎች በበርካታ አካባቢዎች ቢሮዎቹን በኃይል ሰብረው መግባታቸውንም ገልጧል። አንጃው፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ኡመር ሰላማዊ ፖለቲካ ለማካሄድ የሚያስችለውን የመጨረሻውን በር ጥርቅም አድርገው ዘግተውታል በማለት ከሷል።
ሙስጠፋን በሶማሌ ሕዝብ ላይ በመጫን የሰላም ስምምነት ከንቱ ሆኖ እንዲቀር ያደረጉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ናቸው በማለትም አንጃው ወቅሷል።
ይሄው የኦብነግ) አንጃ፣ የሶማሌ ክልል የተወሰኑ የአገር ሽማግሌዎች ዛሬ ሙስጠፋ ስብሰባ ላይ በነበሩበት የአዲስ አበባው ስካይ ሆቴል ፊት ለፊት ተቃውሞ ማሠማታቸውንም ገልጧል።