የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሱማሊያ ምን ይዞ እንደሚመጣ አላውቅም የሱማሊያው ፕሬዝዳንት

የሱማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ፣ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ለሱማሊያ ምን ይዞ እንደሚመጣ ርግጠኛ መኾን እንደማይችሉ ከዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ጋር ባደረጉት አጭር ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።

ኾኖም በፕሬዝዳንት ትራምፕ ዙሪያ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች አሜሪካ ለሶማሌላንድ የአገርነት እውቅና እንድትሠጥ እንደሚፈልጉ ፕሬዝዳንት ሞሐመድ ጠቁመዋል። ፕሬዝዳንቱ፣ የአፍሪካ አገራት ድንበሮች የሚቀየሩ ከኾነ ትልቅ ችግር ይፈጠራል በማለት አስጠንቅቀዋል።

ከአልሸባብ ጋር የሚደረገው ውጊያ አኹንም አስቸጋሪ እንደኾነ ያመኑት ፕሬዝዳንት ሞሐመድ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሥልጣን ዘመን በድጋሚ የሱማሊያ ወታደሮችን ለማሠልጠን የተሠማሩትን የአሜሪካ ወታደሮች እንዳያስወጡ ጠይቀዋል።

ይልቁንም በፕሬዝዳንት ትራምፕ የሥልጣን ዘመን አልሸባብን ለማሸነፍ አሜሪካ የወታደሮቿን ቁጥር እንድትጨምር እንደሚፈልጉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።