የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በአፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ለርዕደ መሬት ጉዳት የተጋለጡ 85 ሺሕ ሰዎች ወደሌሎች አካባቢዎች እየተዛወሩ መኾኑን አስታውቋል።
ከተነሺዎቹ መካከል 55 ሺሕ ያህሉ ከአፋር ክልል ሲኾኑ፣ 30 ሺሕ ያህሉ ከኦሮሚያ ክልል እንደኾኑ ቢሮው ጠቅሷል።
ቢሮው፣ በኹለቱ ክልሎች በጠቅላላው 90 ሺሕ ሰዎች ለርዕደ መሬት ጉዳት ተጋላጭ እንደኾኑ ጠቅሷል።
በአፋር ክልል፣ ለተነሺዎች የተመረጡ የሠፈራ ቦታዎች እንዲቀየሩና ከስጋት ነጻ የኾኑ አዳዲስ የሠፈራ ቦታዎች እንዲለዩ የሠመራና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ እንደሠጡና ተነሺዎችም ወደ አዲሶቹ ሠፈራ ጣቢያዎች እንደሚጓጓዙ ተገልጧል።