የብልጽግና ፓርቲ ደጋፊችና ተሳዳቢዎች በኤርትራ ላይ በየቀኑ “የስድብ መዓት በማውረድ” እና “የስም ማጥፋት ዘመቻ” በማካሄድ ተጠምደዋል

የኤርትራው መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገብረመስቀል፣ የኢትዮጵያው ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊችና ተሳዳቢዎች፣ በኤርትራ ላይ በየቀኑ “የስድብ መዓት በማውረድ” እና “የስም ማጥፋት ዘመቻ” በማካሄድ ተጠምደዋል በማለት ወቅሰዋል።

ኤርትራ የኢትዮጵያን ልማት ስታስተጓጉል ቆይታለች የሚል “የስም ማጥፋት” እየቀረበባት እንደሆነ የጠቀሱት የማነ፣ ሆኖም ኤርትራ የቀጠናው አገራት እድገትና ብልጽግና ቢያስመዘግቡ ለቀጠናው ሕዝቦች ጠቃሚ ይሆናል የሚል እምነት እንዳላት  ገልጸዋል።

የማነ፣ የዜሮ ድምር ስሌት የኤርትራ የቀጠናዊ ፖሊሲና የልማት ስሌት አካል እንዳልኾነም ጠቅሰዋል።

“ድብቅ ዓላማን ለማራመድ” ሲባል፣ እነዚህን መሠረታዊ ሃቆች በሐሰት ትርክት ማጥፋት አይቻልም በማለትም የማነ መልዕክታቸውን ቋጭተዋል።