የአብይ ሰራዊት በወለጋ ከኦነሠ እና ከፋኖ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑ ተሰምቷል

የአብይ ሠራዊት ሰሞኑን በምሥራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና እና ኪረሙ ወረዳዎች ከአማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትና ከአማራ ክልል ድንበር ተሻግረው ከሚመጡ ታጣቂዎች ጋር ውጊያዎችን እያደረገ መኾኑን የአካባቢውተሰምቷል።

በተለይ በኪረሙ ወረዳ “በዴሳ”፣ “ሲሬ ዶሮ”፣ “ባጊን” እንዲሁም “ኦፍጪ” ከተባሉ ኦሮሚያ ክልል ከአማራ ክልል ጋር በሚዋሰንባቸው ቀበሌዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ከአማራ ክልል ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ታጣቂዎች በሚያደርስባቸው ተደጋጋሚ ጥቃት ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ታውቋል።