በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ጊዳ ከተማ፣ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዛሬ በፈጸመው ጥቃት ከ150 በላይ ታራሚዎችን ማስመለጡ ተሰምቷል ።
አብዛኞቹ ታራሚዎች፣ በአካባቢው ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩ ታጣቂዎች መኾናቸውን ምንጮች ነግረውናል።
ኹሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ከእስር ቤቱ አምልጠዋል በማለት ነግረውናል።
ቡድኑ፣ በርካታ ክላሽንኮቭ ዘርፎ መውሰዱንም ምንጮች ገልጸዋል።
ይህንኑ ተከትሎ፣ ያመለጡ እስረኞችን ፍለጋ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አሰሳ መጀመራቸውንና ባካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መስፈኑን ምንጮች ጠቁመዋል።