ከአፋር የተነሳ ኃይል በሕወሓት ወታደሮች ላይ ጥቃት አደረሰ

የትግራይ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ አፈንጋጭ ታጣቂ ቡድን ዛሬ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል በማለት ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ቢሮው፣ ታጣቂ ቡድኑ “ጠብጣብ” በተባለ ቦታ ላይ አደረሰው ባለው ጥቃት የአንድ የክልሉ ጸጥታ ኃይል አባል ሕይወት መጥፋቱን ገልጧል።

ይህ አጥፊ ተግባር ከቀጠለ ቡድኑን በሚመሩና በሚያስተባብሩ አካላት ላይ ርምጃ እወስዳለሁ በማለት ያስጠነቀቀው ቢሮው፣ ደም መፋሰሱ ባስቸኳይ ይቁም በማለት ጥሪ አድርጓል።