በጎሐ ጽዮን እና ቱሉ ሚልኪ ከተማ መካከል ከ40 በላይ የአውቶብስ ተጓዦች ታገቱ

ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ በጎሐ ጽዮን እና ቱሉ ሚልኪ ከተማ መካከል ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ትናንት 8 ሰዓት ገደማ ከ40 በላይ የአውቶብስ ተጓዦችን ማገታቸውን ተሰምቷል።

ታጣቂዎቹ እገታውን የፈጸሙት፣ ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል ሲጓዝ በነበረ “ታታ” ተብሎ በሚጠራ አውቶቡስ ላይ እንደኾነ ምንጮች ነግረውናል። ታጣቂዎቹ በዚህ ወቅት አንዲት ሴት መግደላቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።