ትውልዱ የራሱ መስመር አለው!
አዲሱ ትውልድ የገጠመው ጥያቄ ዘመናትን የቆዬ ቢሆንም በአሮጌ ቀመር ተሰልቶ ምላሽ የሚገኝበት አይደለም። በተሸነፈ አስተሳሰብ እና ቀመሩን ባልተረዳ ቡድን ተመርቶ የሚገኝ ድልም አይኖርም።
ትዉልዱ የራሱን የፖለቲካ ፍልስፍና፣ የእሳቤ መነፅር እና እውነት በራሱ መንገድ አንብሮ እና አስርጾ ዘመኑን የዋጀውን መንገድ /መስመር/ ጀምሯል።
ይህ የገጠመዉን አደጋ እና የውድቀት አዙሪት በአማራዊ አስተውሎት የተረዳው ትውልድ የትላንት ግዝፈቱን ከነገ ተስፋው ጋር አስተሳስሮ፣ በዛሬው እውነታ ሳይቆዝም፣ በትናንት ድምቀቱ ውስጥ በቅዠት ተመስጦ ከእውነታው ሳይነጠል በመጓዝ ላይ ነው።
የአማራ ህዝብ የገጠመውን ፈታኝ የህልውና አደጋ ተከትሎ አስተማማኝ ኃይል ሆኖ የወጣው ትውልድ በመላው አማራ ዘንድ ብሔራዊ ቁጭትን በማቀጣጠል ላይ ነው። ብሔራዊ ቁጭቱን በጥብቅ የአመራር ዲስፕሊን እና ባልተቋረጠ የማንቃት ስራ አሳድገን ጠቅላላ ብሔራዊ ንቃት በመፍጠር ወደፊት ፊት መጓዝ ቀጣይ ተልዕኳችን ነው።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!