በኦሮሚያ ክልልና የሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ የድንበር ግጭት

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ አርሲ ዞን ኮኮሳ እና ነንሰቦ ወረዳዎችና የሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ የድንበር ግጭት፣ ሁለት ሰላማዊ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉንና በ7ቱ ላይ አካላዊ ጉዳት መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ጥቃቱን ያደረሱት ከሲዳማው ጉራ ወረዳ የተሻገሩ ታጣቂዎች መኾናቸውንና ጥቃቱን ተከትሎ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል።

ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹን ባፈናቀሉበት ቦታ ላይ ለመስፈር አስበው እንደነበርም ምንጮች ተናግረዋል ተብሏል።

ካሁን ቀደም ከምዕራብ አርሲ ዞን ተሻግረው በአካባቢው ሠፍረው የነበሩ ሰዎች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲመለሱ ተደርጎ እንደነበርም ተገልጧል።