የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የነበረው ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙ እያነጋገረ ነው

” ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን እያስታወስኩ መልካም የሥራ ዘመን እመኛለሁ ” – ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ አቶ ብርሃኑ አዴሎን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አድርጎ ሾሟል።

ኢሰመኮ ፥ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተሾሙት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከዚህ ቀደም በተለያዩ መንግሥታዊ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ?መሆኑን ከእነዚህም መካከል ፦

  • የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር፣
  • የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር
  • የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እንደነበሩ አስታውሷል።

ተቋሙን በተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፥ ወቅታዊ የሀገሪቱ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ጠንካራ አመራር እና ውጤታማ የሰብአዊ መብቶች ሥራ የሚጠይቅ መሆኑን አስታውሳዋል።

የኢሰመኮን ኮሚሽነሮች እና ባልደረባዎች በመወከል ለዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ከወዲሁ “ መልካም የሥራ ዘመን እመኝላቸዋለሁ ” ብለዋል። የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የነበረው ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙ እያነጋገረ ነው