የታጠቁ ግለሰቦች መቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው ነበር ተባለ

የታጠቁ ግለሰቦች መቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው ነበር ተባለ

በትግራይ ክልል ባለስልጣናት መሀል እየተካረረ የመጣውን ውዝግብ ተከትሎ በዛሬው እለት የታጠቁ ግለሰቦች የመቐለ ኤፍኤም 104.4 ሬድዮን ለመቆጣጠር ሙከራ አርገው እንደነበር ታውቋል።

ሙከራው የተካሄደው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው ቡድን አባላት መሆኑን ነበር ፤  ሙከራው ግን ያልተሳካ ነበር ብለውታል።

“ታጣቂዎቹን ወደ ሬድዮ ጣቢያው ይዞ የገባው በእነ ዶ/ር ደብረፅዮን የተሾመ ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ የተባለ ግለሰብ ነው” ያሉት ምንጫችን ድርጊቱ ሲከሽፍ የኤፍኤም ሬድዮ ጣቢያውን ማህተም ይዘው ሲወጡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቁመዋል።

በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የሕወሓት ክንፍ አባል የኾነው ግለሰብና ታጣቂዎቹ፣ ከጣቢያው ሠራተኞች ማኅተም በመንጠቅ ሠራተኞችን ስብሰባ ጠርተው እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል። ግለሰቡ ወደ ጣቢያው ያመራውና ውዝግብ የተፈጠረው፣ የደብረጺዮን ቡድን ለመቀለ ከተማ የሾማቸው ምክትል ከንቲባ ረዳኢ በርኸ ጣቢያውን እንድመራ ሾመውኛል በማለት እንደኾነ ተገልጧል።