አብይ አሕመድ በመብት ተሟጋች በሲቪል ማኅበራት ላይ የጣለውን እገዳ እንዲያነሳ ውትወታው ቀጥሏል

ሂውማን ራይትስ ዎች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን ጨምሮ በመብት ተሟጋች በሲቪል ማኅበራት ላይ በቅርቡ የጣለውን እገዳ እንዲያነሳና ሲቪል ማኅበራትን ዒላማ ከማድረግ እንዲቆጠብ ጠይቋል።

መንግሥት በሲቪል ማኅበራቱ ላይ የወሰደው ርምጃ ከሲቪል ማኅበራት አዋጁ ጋር እንደማይጣጣም የገለጠው ድርጅቱ፣ ርምጃው መንግሥት የዘፈቀድ እስሮችን ጨምሮ ትችትን ለማፈን ሲያደርጋቸው የቆዩ ጥረቶች አንድ አካል ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ መንግሥት የመብት ተሟጋቾችን ዒላማ ማድረጉን በአጽንዖት እንዲቃወሙትና የኢትዮጵያ ዓለማቀፍ አጋሮች በተለይም አሜሪካና ፈረንሳይ ሲቪል ማኅበራት በአገሪቱ ላላቸው ሚና ድጋፋቸውን እንዲገልጡና እገዳዎቹን እንዲያወግዙም ድርጅቱ ጥሪ አድርጓል።