በአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላን እና የወታደራዊ ሂሊኮፕተር በአየር ላይ ተላትመው ተከሰከሱ።

በአሜሪካ የመንገደኞች አውሮፕላን እና የወታደራዊ ሂሊኮፕተር በአየር ላይ ተላትመው ተከሰከሱ።

አደጋው ያጋጠመው በዋሽንግቶን ዲሲ በሀገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ምሽት 3:00 ላይ ነው።

የፒኤስኤ ንብረት የሆነው የበረራ ቁጥሩ 5342 የሆነና 60 መንገደኞችን እና 4 የበረራ ሰራተኞችን የያዘው አውሮፕላን ሬገን ዋሽንግተን ብሔራዊ ኤርፖርት ለማረፍ በተቃረበበት ሰዓት ነው 3 የአሜሪካ ጦር አባላትን ከያዘ ወታደራዊ ሂሊኮፕተር (ብላክ ሀውክ) ጋር የተላተመው።

አውሮፕላኑ እና ሂሊኮፕተሩ ‘ ፖቶማክ ወንዝ ‘ ላይ ነው የተከሰከሱት።

አደጋውን ተከትሎ የነፍስ አንድ ስራ እየተሰራ ሲሆን የሬገን ኤርፖርት ለጊዜው የአውሮፕላን በረራ ማድተናገድ አቁሟል።

የዲሲ ፖሊስ እስካሁን ስለ ሞቱ ሰዎች የተረጋገጠ መረጃ እንደሌለና የነፍስ አድን ስራ ላይ ርብርብ እየተደረገ እንደሆነ ገልጿል።

የአይን እማኞች ግጭቱ ሲፈጠር ከፍተኛ ብርሃን በአካባቢያቸው ታይቶ እነበር ጠቁመዋል።

የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ” አሰቃቂ አደጋ ” ሲሉ ገልጸው የተሰማቸውን ሀዘን አካፍለዋል።

ምክትል ፕሬዜዳንት ጄዲ ቫንስ ከአሰቃቂው አደጋ ሰዎች እንዲተርፉ ሁሉም በፀሎት እንዲተጋ ጥሪ አቅርበዋል።

የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሮሊን ሌቪት በኤክስ ገጻቸው ላይ ” እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር ” ብለዋል።

መረጃው ከኤስቢኤስ፣ ኒውስኤክስ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

ቪድዮ ፦ avgeekjake