በጎጃም አካባቢዎች በመምህራንና ተማሪዎች ዕገታ ምክንያት ዘንድሮ ማስተማር ጀምረው ያቆሙ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንና በርካታ ተማሪዎች በወላጆች ላይ በሚደርስባቸው ማስፈራሪያ ሳቢያ ትምህርት እያቋረጡ ነው።
በርካታ የገጠር ትምህርት ቤቶች መምህራን፣ ርዕሳነ መምህራንና የትምህርት ተቆጣጣሪዎች በየጊዜው ፋኖ ነን በሚሉ ታጣቂዎች ይታገታሉ ። እነዚህ ፋኖ ነን የሚሉ ታጣቂዎች የታጠቁት መሳሪያ በመንግስት የተደራጁ ናቸው የሚሉ መረጃዎች በሕዝቡ ዘንድ ይነገራል።
ባንዳንድ አካባቢዎች ዕገታውን በመፍራት ወደ ትምህርት ቤት የማይገቡ መምህራን ደሞ፣ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እንደሚታሠሩ ምንጮች ገልጸዋል።
በክልሉ የዚህ ዓመት የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ድረስ መራዘሙን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ትናንት አስታውቋል።