በኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች፣ በግብር ስም በየጊዜው እንዲከፍሉ የሚጠይቁት ገንዘብ እንዳማረራቸው ተናግረዋል።
በክፍለ ከተማው፣ “ለልማት”፣ “ለሚሊሻ”፣ “ለመኖሪያ ቤት ግብር” በሚሉ ምክንያቶች ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰበሰብ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
አንድ መምህር፣ ካለፈው ዓመት ግንቦት ወር ጀምሮ እስከ ሐምሌ 2016 ዓ፣ም መጨረሻ ባሉት ወራት ውስጥ ብቻ በስንቄ ባንክና በቀበሌ ተወካዮች በኩል 10 ሺሕ ብር ለመንግስት መክፈላቸውን አስረድተዋል።
ደረሰኞቹ፣ ማኅተም እንደሌላቸውና የገንዘብ ተቀባዩም ስም እንዳልተጻፈባቸው ታውቋል።