ለእስክንድር ነጋ ወርቅነህ ገበየሁና ኃይሉ ጎንፋ የመንግሥት አካላት አይደሉም!( አቻምየለህ ታምሩ)

“የመንግሥት አካል” የሌለበቱ እስክንድር ነጋ ከአፍሪካ ኅብረትና ኢጋድ ያደረገው “ውይይት”¡ ( አቻምየለህ ታምሩ)

እስክንድር ነጋ በምላስና ጆሮዎቹ በኩል እንደነገረን ከሰሞኑ ከአፍሪካ ኅብረትና ከኢጋድ ጋር አደረግሁት ባለው “ውይይት” “የመንግሥት አካል የለበትም” ሲል ነግሮናል።

ሆኖም ግን እስክንድር ነጋ በዐቢይ አሕመድ ላኪነት የተገናኘው ወርቅነህ ገበዬሁ ከሚመራው ኢጋድና ኃይሉ ጎንፋ ከሚዘውረው የአፍሪካ ኅብረት የጸጥታ ክፍል ጋር ነው።

ከታች በሚታየው ምስል በስተግራ በኩል የሚታየው የአፍሪካ ኅብረት (AU) የጸጥታ ኃላፊ ተደርጎ ዐቢይ አሕመድ የአፍሪካ ኅብረት ሰብሳቢ በነበረበት ወቅት የተሾመው የኦነግ አበጋዝ የሆነው ኃይሉ ጎንፋ ነው።

በስተቀኝ በኩል የሚታየው ደግሞ ዐቢይ አሕመድ የኢጋድ ሰብሳቢ በነበረበት ወቅት የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ተደርጎ የተሾመው የኦሕዴዱ ወርቅነህ ገበዬሁ ነው።

እስክንድር ነጋ ከኢጋድና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር አደረግሁት ባለው “ውይይት” ውስጥ “የመንግሥት አካል የለም” የሚለን ወርቅነህ ገበዬሁና ኃይሉ ጎንፋ ከሚመሩት ከኢጋድና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያደረገውን አውጫጭኝ ነው። ለእስክንድር ነጋ ወርቅነህ ገበየሁና ኃይሉ ጎንፋ የመንግሥት አካላት አይደሉም!