የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች ጊዜያዊ አስተዳደሩ በአዲስ እንዲዋቀር መወሰናቸውን አሳወቁ

የትግራይ ወታደራዊ አመራሮች ጊዜያዊ አስተዳደሩ በአዲስ እንዲዋቀር መወሰናቸውን አሳወቁ

ራሳቸውን የትግራይ ኃይል አመራሮች ብለው የሚጠሩት እነዚህ የክልሉ መኮንኖች ለቀናት ካደረጉት ስብሰባ በኋላ ሐሙስ ጥር 15/2017 ዓ.ም. መቀለ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ነው የጊዜያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር ውሳኔ ማሳለፋቸውን ያሳወቁት።

በፕሪቶሪያ ስምምነት መሠረት የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ኃላፊነቱን በአግባቡ አልተወጣም በማለት የሌሎች መጠቀሚያ ሆኗል የሚል ብርቱ ክስ አቅርበዋል።

በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በወታደራዊ አመራሮቹ ስለቀረበበት ክስ እና ስላሳለፉት ውሳኔ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

በመግለጫው በጊዜያዊ አስተዳደሩ “ቁልፍ ሥልጣን የነበራቸው አመራር እና አባላት ከተሰጣቸው ተልዕኮ ውጪ የሕዝብን ጥቅም ወደ ጎን በመተው ክህደት በመፈጸም የውጭ ኃይል መሣሪያ ሆነዋል” ብሏል።