የኖርዌይ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ባስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዙ ተሰማ

የኖርዌይ መንግሥት ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ጨምሮ በአገሪቱ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ባስቸኳይ እንዲወጡ ማዘዙን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ኖርዌይ፣ የውጭ ዜጎችን መውጣት እውን ለማድረግ፣ ከመነሻ አጋራቸው ጋር በትብብር ለመስራት ጥረት እያደረገች መኾኗን ባለሥልጣናቷ መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

አውሮፓ ኅብረት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹን ለሙቀበል ትብብር አላሳየም በማለት፣ ከወራት በፊት በኢትዮጵያዊያን ላይ ጠበቅ ያለ የቪዛ ገደብ መጣላቸው ይታወሳል።

ኾኖም የኢትዮጵያ መንግሥት ኖርዌይ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት በስደተኛ መጠለያዎች የኖሩ የተወሰኑ ስደተኞችን እንደተቀበለ የጠቀሱት ዘገባዎቹ፣ መንግሥት በዚኹ ትብብሩ ከቀጠለ ኖርዌይ በኢትዮጵያዊያን ላይ የጣለችውን የቪዛ ገደብ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት ልታነሳ እንደምትችል መጠቆሟን ጠቅሰዋል።