አሜሪካ በሱዳን ወታደራዊ መሪ ጀኔራል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ ጥላለች።

አሜሪካ፣ በሱዳን ወታደራዊ መሪና በጦር ሠራዊቱ ዋና አዛዥ ጀኔራል ቡርሃን ላይ ትናንት ማዕቀብ ጥላለች።

አሜሪካ በጀኔራል ቡርሃን ላይ ማዕቀብ የጣለችው፣ ከድርድር ይልቅ የጦርነት አማራጭን መርጠዋል በማለት ነው።

ጄነራል ቡርሃን የሚመሩት ሠራዊት፣ በሲቪል መሠረተ ልማቶች ማለትም በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎችና በገበያ ቦታዎች ላይ ጥቃቶችን እና ከፍርድ ውጭ የኾኑ ግድያዎችን ይፈጽማል በማለት አሜሪካ ከሳለች።

ለሱዳን ጦር ሠራዊት ጦር መሳሪያ ያቀብላሉ የተባሉ አንድ የሆንግኮንግ ኩባንያና አንድ የሱዳንና ዩክሬን ተወላጅ ግለሰብም የማዕቀቡ ሰለባ ኾነዋል።

ማዕቀቡ የንብረትና ገንዘብ የማንቀሳቀስና ማንኛውም አሜሪካዊ ዜጋና ኩባንያ ጋር የንግድ ልውውጥ እንዳያደርጉ የሚያግድ ነው።

አሜሪካ፣ በፈጥኖ ደራሹ ኃይል ዋና አዛዥ ጀኔራል ደጋሎ ላይ ከቀናት በፊት ተመሳሳይ ማዕቀብ እንደጣለች ይታወሳል።