አብይ አሕመድ በመጭው ምርጫ ፖለቲካ ፓርቲዎችን ጠልፎ ለመጣል የሚያስችል አዋጅ እንዲረቀቅ አዘዋል፤ በዚህም መሰረት ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አዋጅ ረቂቅ ማሻሻያ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
ረቂቅ ማሻሻያው፣ ቦርዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አዋጅ የሚጥሱ ፓርቲዎችን ሕጋዊነት ከመሰረዙ በፊት በጥፋቱ ክብደት ልክ እስከ 5 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ማገድ የሚያስችለውን ሥልጣን የሚሠጥ ነው።
ቦርዱ የጣለበትን እገዳ የተቃወመ ፓርቲ፣ ውሳኔው በደረሰው በ30 ቀናት ውስጥ ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችል የተሻሻለው አዋጅ ይፈቅዳል።
ቦርዱ አገራዊ ምርጫ ማካሄድ የማይችልባቸው “ኹኔታዎች” የሚለው አንቀጽም፣ የጸጥታ ችግር፣ ወረርሺኝ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ተብሎ ተዘርዝሯል።
ለሕዝብ ተወካዮችና ለክልል ምክር ቤቶች ምርጫ የተመዘገቡ ዕጩዎች ከባድ ወንጀል ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ ካልተያዙ በስተቀር፣ የምርጫው ውጤት እስኪገለጽ በወንጀል ተጠርጥረው እንዳይያዙ የሚከለክል አንቀጽም በማሻሻያው ተካቷል። አዲሱ የምርጫ ቦርድ ማሻሻያ አዋጅ በመጭው ብርጫ እሸነፋለሁ ብሎ የሰጋው አብይ አሕመድ የፃፈው መሆኑ ታውቋል።