መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ ጨመረ

መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በወጪ መጋራት ፖሊሲ የሚከፍሉትን ክፍያ እስከ አምስት ዕጥፍ ገደማ እንደጨመረው ተሰምቷል ።

የወጪ መጋራት ክፍያ የተጨመረው፣ የአንድ ተማሪ የቀን የምግብ በጀት ከ22 ብር ወደ 100 ብር መጨመሩን ተከትሎ ነው።

በአዲሱ ማስተካከያ መሠረት፣ ለአራት ዓመት የዩንቨርሲቲ ቆይታ አንድ ተማሪ ይከፍለው የነበረው ከ25 ሺሕ ብር የማይበልጥ ክፍያ ወደ 120 ሺሕ አሻቅቧል።

35 ሺሕ ብር ገደማ ይከፍሉ የነበሩት አምስት ዓመት የሚማሩ የምህንድስና ተማሪዎች ደሞ ወደ 150 ሺሕ ብር አካባቢ እንዲከፍሉ ይደረጋል።

ትምህርት ሚንስቴር አዲሱን የወጪ መጋራት ተመን ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገና ባይልክም፣ በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ታውቋል።