በማይናማር በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ታጉረው ከወር በላይ እንደቆዩ የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን ጥሪ አቀረቡ፡፡

በማይናማር በወታደራዊ ካምፖች ውስጥ ታጉረው ከወር በላይ እንደቆዩ የሚናገሩ ኢትዮጵያዊያን፤ ‘’መንግስት ይድረስልን’’ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ተታለው ወደ ማይናማር የሄዱና በዚያም በማይከፈላቸው ህገ ወጥ ስራዎች እና በስቃይ ውስጥ እንደቆዩ የሚናገሩት ኢትዮጵያዊያን ከዚያ ህይወት ወጥተው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እየተጠባበቁ ቢሆንም መንግስት ቶሎ ሊደርስልን አልቻለም ሲሉ ለሸገር ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በዚያው በማይናማር በዲኬቤና ሌላም ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ተጠልለው ያሉት ኢትዮጵያውያን በቁጥር ከ700 በላይ ነን ብለዋል፡፡

በቦታው ውሃ እና ምግብ በአግባቡ እንደማይቀርብላቸው እና ለበሽታም እየተጋለጡ መሆኑን ነግረውናል፡፡

‘’መንግስት ይድረስን’’ የሚል ጥሪ ያቀረቡት ስደተኞቹ ከዚህ ቀደም ህገ-ወጥ ስራ ያሰሩን ነበር እየደበደቡም እያሰቃዩን ነበር ያሏቸው ግለሰቦች እየመጡ እንደገና ወደነበርንበት ስቃይ እንድንመለስ የካምፑን ሀላፊዎች እያነጋገሩ በመሆኑ ስጋት ገብቶናል እያሉ ነው፡፡

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/cgfb/