55 መንገደኞች በኦሮሚያ ታገቱ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ በጎሐጽዮን እና ቱሉ ሚልኪ ከተሞች መካከል በሚገኝ ሥፍራ ላይ ታጣቂዎች ጧት 3 ሰዓት ገደማ በተለምዶ ”ታታ” ተብሎ የሚጠራ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ አስቁመው ከ55 በላይ ተሳፋሪዎችን አግተው መውሰዳቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች። ከእገታው ለማምለጥ የሞከሩ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልተገለጸ ተሳፋሪዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን ምንጮች ተናግረዋል። አውቶቡሱ እገታ የተፈጸመበት፣ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በማቅናት ላይ ሳለ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ ”ፈለገ ግዮን” በተባለ አገር አቋራጭ አውቶቡስ ላይ ተመሳሳይ እገታ ተፈጽሞ፣ 60 ገደማ አካባቢ ተሳፋሪዎች አፍነው መወሰዳቸውን ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል።